Fana: At a Speed of Life!

ቻይና እና ሩሲያ በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመደጋገፍ እንደሚሰሩ በድጋሚ አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ወሳኝ በሆኑ የጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመደጋገፍ እንደሚሰሩ አረጋገጡ፡፡

ከውይይታቸው በኋላ መሪዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ፥ ሀገራቱ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዘላቂ ልማት ላይ በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ሀገራቱ በውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ የሚገባ ማንኛውንም የውጭ ኃይል በጥብቅ እንደሚያወግዙም ነው ያሳወቁት፡፡

የውጭ ኃይሎች በሀገራቱ አጎራባች ቀጠና ያለውን ጸጥታና ደኅንነት ለመናድ የሚያደርጉትን ሙከራም እንዲያቆሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስጠንቅቀዋል።

ዓለማችን በለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ የገለጸው መግለጫው፥ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለውጡን የሚመጥን አስተማማኝ ሠላምና ዘላቂ ልማት እንደሚያሻውም ጠቁሟል፡፡

ሀገራት መብትና ጥቅሞቻቸውን ለመጉዳት ከሚንቀሳቀሱ ኃይላት እራሳቸውን እንዲጠበቁ እና የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የጋራ እሴቶች የሆኑት ሠላም፣ ልማት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ዴሞክራሲ እና ነፃነት በየትኛውም ኃይል እንዳይገረሰሱ በጋራ ዘብ እንዲቆሙ ቻይና እና ሩሲያ በጋራ መግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

ለተባበሩት መንግስታት ድርጅትም የዓለም አቀፉን ሥርዓት እና ህግ እንዲያስከብር ጥሪ አቅርበዋል።

ቻይና እና ሩሲያ ከሀገራቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚስማማ የዴሞክራሲ ስርዓት ያላቸው በመሆኑ ዴሞክራሲያቸው የሚለካው በሀገራቱ ህዝቦች ጥቅምና ፍላጎት ብቻ እንደሆነም አስምረውበታል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በርካታ የትብብር ሰነዶችን እንደተፈራረሙም ነው ሲጂቲ ኤን በዘገባው ያመላከተው፡፡

በዓለማየሁ ገረመው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.