Fana: At a Speed of Life!

የእጩ ኮሚሽነሮች ምርጫ ኢትዮጵያዊ ብዝኃነትን ያካተተ እንዲሆን ተሞክሯል-አፈ ጉበዔ ታገሳ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮችን ለመምረጥ በተደረገው ሂደት ኢትዮጵያዊ ብዝሃነትን ያካተተ እንዲሆኑ ለማስቻል ጥረት መደረጉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉበዔ ታገሳ ጫፎ ገለጹ።
 
አፈ-ጉበዔው እጩ ኮሚሽነሮችን አስመልክቶ ለሕዝብ አስተያየት መስጫ በተዘጋጀ መድረክ ላይ እንደተናገሩት÷እጩ ኮሚሽነሮቹ ለዚህ ታሪካዊ ሃላፊነት ሲታጩ በአገራችን አንድነትና በኢትዮጵያዊነት መሰረት ቆመው ውይይትና ምክንያትን መሠረት ያደረጉ አገራዊ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮችን በመለየት ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
 
በመርሃ ግብሩ በእጩ ኮሚሽነሮች ተአማኒነት፣ የብሄር ተዋጽኦ፣ ከፖለቲካ አመለካከት እንዲሁም የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎ ምን መምሰል አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ተገልጿል፡፡
 
እጩ ኮሚሽነሮቹ ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር መፍታት የሚችሉ፣ በጥናትና ምርምር የተደገፉ፣ ጥርጣሬን ማስወገድ የሚችሉ፣ ከመንግስት ጥገኝነት የተላቀቁ እና ሁሉንም ማህበረሰብ ያቀፉ እንዲሆኑም የጉባዔው ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።
 
በመድረኩ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ የሲቪክ ማኅበራት ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና የሀገር ሽማግሌዎች መሳተፋቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.