Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)   የካንሰር በሽታን የመከላከል አቅምን ለማሻሻል በዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ዳይሬክተር የተነደፈ ተነሳሽነት ይፋ ሆነ።

የካንሰር በሽታን የመከላከል አቅምን ለማሻሻልና የአፍሪካ ሀገራትን ቅድሚያ ተጠቃሚ ለማድረግ የተነደፈው የዳይሬክተሩ ኢኒሼቲቭ በአፍሪካ ህብረት ግቢ ውስጥ ይፋ ሆኗል።

ኢኒቬቲቩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ፣ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር፣ የሴኔጋል፣ የማላዊ እና የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ካንሠርን ለመከላከል የተቀረፀውን ይህንን ኢኒሸቲቭ ለስኬት እንዲበቃ  እንደሚሰሩ በመግለፅ ከአለማቀፍ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ጋር ስምምነት ፈርመዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተነሳሽነቱ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ የሚገኘውን የካንሰር የጨረራ ህክምና በማስፋት ሀገራችንን ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ጥቅም ለማዋል ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ሃይል ኤጀንሲ ጋር በቅርበት እየሰራች መሆኑን መናገራቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጅ ተቋም በኢትዮጵያ በእርሻ፣ ጤና፣ ትምህርት እንዲሁም በተለያዩ የልማትና የኢኮኖሚ ዘርፎች ለሚሠራው ስራ ቀዳሚ የመገናኛ ቢሮ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.