Fana: At a Speed of Life!

ሕብረቱ አፍሪካ በተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ በምታገኝበት ሁኔታ ላይ መከረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀጥታው ም/ቤት ለአፍሪካ የውሳኔ ሰጪነት ቦታን መስጠት የሚያስችለው ሪፎርም እንዲያደርግ የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አፅንኦት ሰጥቶ መምከሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደር ዲና ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አፍሪካ በዓለም አቀፉ መድረክ ከውሳኔ ሰጪዎች አንዷ መሆኗ የግድ እውን ሊሆን እንደሚገባ መስማማታቸውን ገልጸዋል።

በመሪዎቹ ጉባኤ ላይ ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዘላቂ የግብርና ልማት ላይ ያቀረቡት አንዱ መሆኑን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ የበጋ መስኖ ልማትና አረንጓዴ አሻራን በተመለከተ ያላትን ተሞክሮ አጋርተዋል ነው ያሉት።

አልጄርያ የፀረ ሽብርተኝነት ተግባረትን፤ ሰላምና ፀጥታን የተመለከተ፣ የአፍሪካ 2063 አጀንዳ ያለበትን ደረጃ ደግሞ ኮትዲቯር ሪፖርት ማቅረባቸውንም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በበርናባስ ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.