Fana: At a Speed of Life!

የሴኔጋል ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ማኪ ሳልን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት ሲካሄድ በቆየው 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህብረቱ ሊቀመንበርነትን የተረከቡት የሴኔጋል ፕሬዚዳንት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ፕሬዚዳንቱን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በተጨማሪም የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ኒየሲ፣ የጋምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አይሳቱ ቶሬይ እና የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፊሊፕ ሚያፓንጎ በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ፕሬዚዳንቶቹን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
በጉባኤው ተሳታፊ የነበሩ የሀገራት መሪዎችም ወደ ሀገራቸው ተመለሱ ሲሆን÷ የተመለሱ መሪዎች መካከል የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሲሼኬዲ፣ የጋና ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ፣ የኮቲዲቯር ፕሬዚዳንት አላሳን ኦታራ፣ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ሙሐማዱ ቡሃሪመሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ይገኙበታል።
በተጨማሪም የሞሪታኒያ፣ ኮንጎ፣ የኮሞሮስ፣ የቤኒን፣ የኮንጎ ሪፐብሊክ፣ የኒጀር፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ የሲሸልስ፣ የዛምቢያ፣ የኡጋንዳ፣ የጋቦን፣ የሞዛምቢክ፣ የማላዊ፣ የኬፕ ቨርዴ፣ የዝምባዋብዌ፣ የታንዛኒያ እና የፍልስጤም መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.