Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የፀዳ አስተሳሰብ በመያዝ ህዝብን በአገልጋይነት ስሜት ማገልገል እንደሚጠበቅበት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አመራሩ ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የፀዳ አስተሳሰብና አመለካከት በመያዝ ህዝብን በአገልጋይነት ስሜት ማገልገል እንደሚጠበቅበት የሲዳማ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አሳሰቡ፡፡
የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሀዋሳ ከተማ በተካሄደ መድረክ፥ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች በመመራት የሽብር ቡድኖችን የሚደግፉ እና የተሳሳቱ አስተሳሰቦችና አመለካከቶች የሚስተዋልባቸው አንዳንድ አመራሮች ጎራቸውን እንዲለዩ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። በቀጣይ የማጥራት ሥራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
“መመረጥ ተለውጦ ሀገርን ለመለወጥ” በሚል መሪ ሀሳብ በሀዋሳ ከተማ የመካከለኛ አመራሮች የምክክር መድረክ ሲካሄድ አፈ ጉባኤዋ ባደረጉት ንግግር፥ በህወሓት አሸባሪ ቡድን የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት፣ተጎጂዎችን መልሶ ለመቋቋም እና የስራ አጥነት ችግሮችን ለመፍታት የአመራሮች ቍርጠኝነት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡
አመራሩ ከጎጠኝነትና ከዘረኝነት የፀዳ አስተሳሰብና አመለካከት በመያዝ ህዝብን በአገልጋይነት ስሜት ማገልገል እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡
የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው÷ ውይይቱ ዕቅዶችን ተግባር ላይ በማዋል ሀገርን መለወጥ እንዲቻል በአስተሳሰብና አመለካከት የጎለበተ አመራር እንዲኖር እንደሚያስችል ጠቁመው፥ መሰል የምክክር መድረኮች በክልሉ 37ቱም ወረዳዎች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በታምራት ቢሻ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.