Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ሥልጠና ዛሬ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ መድረክ ሥልጠና ተጀምሯል፡፡
አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመራር ብቃትና አስተሳሰብ እንዲያጎለብትና የመረጠውን ህዝብ በትጋትና በቅንነት እንዲያገለግል ያለመ መድረክ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
መድረኩ ጥንካሬዎችንና መልካም አፈጻጸሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ውስንነቶችን ደግም ነቅሶ በማረም ህዝቡ በሚጠብቀው ደረጃ ለማገልገል የሚያስችል የአመራር አቅም ለማጎልበት የተዘጋጀ ነው መባሉን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚካሔደው በዚህ የአቅም ግንባታ መድረክ ላይ ከ320 በላይ አመራሮች ሚስትሮችና ሚስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል ተቋማት ሃላፊዎችና ምክትል ሃላፊዎች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.