Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለተከሰተው ድርቅ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ 327 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተመድ ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ ለተጎጂዎች የሰብዓዊ እርዳታ እና ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎችን ለማቅረብ 327 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገው ተመድ ገለፀ።

በአፍሪካ ቀንድ ለተከታታይ አስርት ዓመታት የከፋ ድርቅ እያጋጠመ መሆኑን የጠቆመው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፥ አሁን ላይ በኬንያ፣ ሶማሊያ እና ኢትዮጵያ 13 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አንስቷል።

ድርቁ የሰብል ምርትን በማውደሙ እና ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ የእንስሳት ሞት ያስከተለ በመሆኑ ኑሯቸውን በግብርና ላይ ያደረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ቀያቸውን ጥለው እንዲሰዱ አድርጓል ብሏል።

የውሃ እና የግጦሽ መሬት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ እና በመጪዎቹ ወራት የዝናብ መጠን ከአማካይ በታች እንደሚሆን በመተንበዩ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ የበለጠ ስጋት መፍጠሩን በምስራቅ አፍሪካ የአለም የምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ማይክል ደንፎርድ ተናግረዋል።

በፈረንጆች አቆጣጠር 2011 በሶማሊያ እንደተከሰተው እና 250 ሺህ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈውን ዓይነት አደጋ በድጋሚ እንዳይከሰት በፍጥነት ወደ እርምጃ መግባት ያስፈልጋል ማለታቸውን ቲአርቲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.