Fana: At a Speed of Life!

በበጋ የስንዴ ልማት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በሀገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት መስራት ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጋ የስንዴ ልማት የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በሀገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት መስራት ይገባል ሲሉ የዘርፉ ተመራማሪዎች ተናገሩ፡፡
በግብርናው ዘርፍ ከ30 አመት በላይ ጥናትና ምርምር ያደረጉት ዶክተር ካሳሁንዘውዴና ዶክተር ፋንታሁን መንግስቱ እንዳለት፥ ባለፉት 3 አመታት ለመስኖ ልማት የተሰጠው ትኩረት በአጭር ጊዜ በምግብ እራስን ለማቻል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ነው።

በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ካሳሁን እንደሚናገሩት፥ በሀገሪቱ እየናረ ለመጣው የምግብ ዋጋ እና የኑሮ ውድነት የግብርናው ምርታማነት በበቂ ደረጃ አለመሆን ዋነኛ ምክንት ነው ብለዋል፡፡
60 በመቶ የሚታረስ መሬት ባላት አህጉር ሃገራት እስከ 45 ቢሊየን ዶላር ለምግብ ግዢ እንደሚያወጡ የሚያነሱት ዶክተር ካሳሁን የኢትዮጵያ ጅምር ተጠናክሮ ከቀጠለ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ እስከመሆን አቅም አለን ነው ያሉት ።
የግብርና ዘርፍ ተመራማሪው ዶክተር ፋንታሁን በበኩላቸው፥ በበጋ ወቅት ስንዴን በመስኖ ለማልማት ስራዎች በመንግስት ትኩረት መሰጠቱ ትክክለኛ እርምጃ ነው ብለዋል፡፡
ይህ ግብርናውን የማዘመንና ምርቱ በእጥፍ የማሳደግ ጥረት ውጤቱ ደግሞ ከአርሶ አደሩ በላይ በቀጥታ ሸማቹ ጋር የሚደርስና በምግብ እራስን ለመቻል የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም ዘርፉ አሁንም በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራሮች መደገፍ ይኖርበታል ሲሉም ነው የገለፁት ።
ኢትዮጵያ ዘንድሮ በበጋ መስኖ ከለማ ከ400 ሺህ ሄክታር መሬት ከ16 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ትጠብቃለች ።
በሀይለየሱስ መኮንን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.