Fana: At a Speed of Life!

ፈረንሳይ ማሊን ጨምሮ የምዕራብ አፍሪካን አገራት ለመከፋፈል እየሞከረች ነው – የማሊ ጠ/ሚ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ቹጉኤል ማይጋ ፈረንሳይ በልዩ ተልዕኮ የተሰማሩ ወታደሮቿን በመጠቀም የምዕራብ አፍሪካን አገራት ለመከፋፈል እየሞከረች ነው ሲሉ ወቀሱ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዲፕሎማቶች ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ ማሊ ከጽንፈኛ ታጣቂዎች ጋር በተደረገው ጦርነት ለተሰዉ የፈረንሳይ ወታደሮች ትልቅ ክብር እንዳላት አውስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፈረንሳይ ማሊን ለመርዳት በሚል ተልዕኮ አሸባሪዎችን እየረዳች መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

በማሊ ውስጥ በልዩ ተልዕኮ ወታደሮች ልጆቻቸውን ያጡ ፈረንሳውያን የአገራቸው መንግስት ማሊን ከመርዳት ይልቅ አገሪቱን ለሁለት ለመከፋፈል እየሰራ መሆኑን ሊያውቁ ይገባል ነው ያሉት ፡፡

የተዳከሙ አሸባሪዎች ተመልሰው አገራችንን እንዲወሩ ለሁለት ዓመታት ያህል እንደገና እንዲደራጁ እና አቅም እንዲኖራቸው ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች ሲሉም ፈረንሳይን ወንጅለዋል።

በፈረንጆቹ 2013 ላይ የፈረንሳይ ጣልቃ ገብነት በማሊ በጀመረበት ወቅት የፈረንሳይ ጦር አሸባሪዎችን በማሰልጠን እና የቱዋሬግ ተገንጣዮችን ይደግፋል በሚል ክስ አቅርበው እንደነበርም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰዋል።

ይሁን እንጅ በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ የሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲም ሆነ የፈረንሳይ መንግስት በወቅቱ ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠቱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ሰርቫል በመባል የሚታወቀው የፈረንሳይ ወታደራዊ ዘመቻ ሰሜናዊ ማሊን ከጽንፈኛ ታጣቂዎች ለመመለስ እርዳታ ሲያደርግ መቆየቱን አፍሪካን ኒውስ በዘገባው አስታውሷል።

በሚኪያስ አየለ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.