Fana: At a Speed of Life!

ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ዳያስፖራዎች አሶሳ ከተማ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከተለያዩ የዓለም ሀገራት ወደ ሀገር ቤት የመጡ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ዛሬ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ገቡ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ አመንቴ ገሺ ለኢዜአ እንደተናገሩት፥ ዛሬ ከ60 የሚበልጡ ዳያስፖራዎች አሶሳ ከተማ ገብተዋል።

ከዳስፖራዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ያስታወቁት የቢሮ ሃላፊው÷ የክልሉ ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ገለጻ ይደረግላቸዋል ብለዋል።

የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ በሶስት ቀናት ቆይታቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብን እንደሚጎበኙና የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጭ ስፈራዎችን እንደሚመለከቱ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት መግባታቸው የሚታወስ ነው።

ለዳያስፖራዎች የክልሉን የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽን በአሶሳ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ለ3 ቀናት የሚቆየው የፕሮሞሽንና ኤግዚቢሽን መርሃ ግብሩ÷ የክልሉን እምቅ ሃብት ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ያለመ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዳያስፖራዎች በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በማንፋክቸሪኒግ፣ በአገልግሎት፣ በማዕድን፣ ኢንዱስትሪና በእርሻ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩም ጥሪ ቀርቧል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.