Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ምክትል ዋና  ፀሀፊ አሚና መሀመድ በኢትዮጵያ ያደረጉት ቆይታ የግጭቱን አሳዛኝ መልክ እንዳሳያቸው ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ያደረጉትን ቆይታ ተከትሎ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የተመድ ምክትል ዋና  ፀሀፊ አሚና መሀመድ የግጭቱን አሳዛኝ መልክ ተመልክቻለሁ አሉ ።

”ግጭቱ ከወራት በፊት እንደነበረው አይደለም አሁን መጠነኛ መረጋጋት አለው”  ያሉት ምክትል ዋና ፀሀፊዋ፥ ግጭቱ በተከሰተባቸው ቦታዎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ።

በቀጣይ ሀገሪቱ ልታከናውን ያሰበችው የብሔራዊ መግባባት ውይይትም ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መፍትሄ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልፀዋል ።

ምክትል ዋና ፀሀፊዋ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በተለይም በአማራ እና አፋር ክልሎች ባደረጉት ጉብኝት አሸባሪው የህወሃት ቡድን ያደረሳቸውን የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እንደዚሁም ቡድኑ ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል የቀበረበትን የጅምላ መቃብሮች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

በፀጋዬ ወንድወሰንና ሀይለየሱስ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.