Fana: At a Speed of Life!

ከግዙፍ ደታ (ውሂብ) የሚገኘውን ጥቅም በመጠቀም የእድገት ምንጭ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከግዙፍ ውሂብ የሚገኘውን ጥቅም በማወቅና በመጠቀም የእድገታችን ምንጭ ማድረግ ይገባል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ተናገሩ።
በግዙፍ ውሂብ (Big Data) እና የመረጃ ደህንነት ላይ “በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት ወደፊት እንዴት መንቀሳቀስ ይችላሉ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ አገራት ዜጎቻቸውን የተመለከቱ መረጃዎችን ማግኘት ባለመቻላቸው ውሂብን ወደ ሃብት ለመቀየር እንቅፋት ሆኖባቸዋል ብለዋል።
ከግዙፍ ውሂብ የሚገኘውን ጥቅም በማወቅና በመጠቀም የእድገታችን ምንጭ ማድረግ ይገባናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ፥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርም ዘርፉን የሚመለከቱ የህግ ማዕቀፎችን እያዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።
የግዙፍ ውሂብ ጥቅምን ማወቅና ተንትኖ ለሚፈለገው ጥቅም ማዋል ላይ ወደ ኋላ መቅረት፣ በተቋማትም ሆነ በግለሰቦች መካከል የሃብትም ሆነ ሌሎች ልዩነቶች እየሰፉ መሄዳቸው ስለማይቀር ሰፊ ስራ መስራት ይጠይቃል ተብሏል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ተከታታይ የበይነ መረብ ውይይት አካል በሆነው በዚህ ውይይት ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የግል ዘርፍ አንቀሳቃሾች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች እና በውጭ ሀገር የሚገኙ ታዳሚዎች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.