Fana: At a Speed of Life!

የአማራና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ርዕሳነ-መስተዳድሮች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድሩ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፥ በሁለቱም ክልል ህዝቦች ህገ-መንግሥቱን መሠረት በማድረግ የህዝብ ለህዝብ ግንኘነት በማጠናከር የተጀመሩ የውይይት መድረኮችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተናግረዋል።

የሁለቱንም ክልል ህዝቦች የጋራ የሠላምና ልማት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጋራ ዕቅድ በማወጣት የፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን ከመሥራት ጎን ለጎን የሠላምና የጸጥታ ሥራዎችን አጠናክሮ በመስራት ለህዝቦች የሠላምና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ነው የገለፁት።

አቶ አሻዲሊ ሀሠን በበኩላቸው÷የቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልል ህዝቦች የጋራ የሠላምና የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በባለፋት ጊዚያት ዘርፈ-ብዙ ሥራዎች ሲስሩ ቆይተዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የሁለቱን ክልልች ህዝቦች ለዘመናት የቆየውን ወንድማማችነትና አብሮነት ይበልጥ ትስስሩን በማጠናከር የጋራ ሠላምና የልማት ጠቃሚነትን ለማጎልበት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ርዕሰ-መስተዳድሩ አያይዘውም፥ በክልሉ በመተከል ዞን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እና በአካባቢው ዘላቂ ሠላምና ልማትን ለማረጋገጥ የጸጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየከፈሉት ላለው መስዋእትነት የላቀ ምስጋና አቅርበው እንደ አገር ብሎም እንደ ክልል የገጠሙንን ፈተናዎች ተቀራርቦ በመስራት ችግሮችን በአሸናፊነት ልንወጣ ይገባል ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.