Fana: At a Speed of Life!

ኢራን አዲስ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣የካቲት 2፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢራን ኬይባር ሼይካን የተሰኘ አዲስ የረጅም ርቀት ሚሳኤል ይፋ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
የረጅም ርቀት ሚሳኤሉ የኢራን ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል መሀመድ ባገሪ እና ሌሎች ወታደራዊ ባለስልጣናት በተገኙበት ነው ይፋ የተደረገው፡፡
1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘገው ይህ ሚሳኤል ከኢራን የረጅም ርቀት ሚሳኤል ፕሮጅክቶች አንዱ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ ምዕራባውያን ይፋ ካደረጓቸው የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ጋር የሚስተካከል አቅም እንዳለው ተመላክቷል፡፡
ይፋ የተደረገው አዲሱ የጦር መሳሪያ ጠጣር ነዳጅ እንደሚጠቀም እና ክብደቱም ከሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር ሲነፃፀር በአንድ ሶስተኛ ያነሰ ነው ተብሏል፡፡
ኢራን ከአሜሪካ የሚጣሉባትን ተደጋጋሚ ማዕቀቦች ተከትሎ ወታደራዊ አቅሟን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከረች መሆኑን አር ቲ በዘገባው ጠቁሟል፡፡
አገሪቱ በተለይ ባለፈው ዓመት የመከላከል አቅሟን ለማሳየት፣ በርካታ ወታደራዊ ልምምዶችን እንዲሁም ያላትን የጦር መሳሪያ ዝግጅት ለዜጎች ይፋ ስታደርግ ቆይታለች።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.