Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን ከ2 ሺህ ቶን በላይ የሰብአዊ እርዳታ ለገሰች

አዲስ አበባ፣የካቲት 2፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሆን ከ2 ሺህ ቶን በላይ የሰብዓዊ ርዳታ ድጋፍ ማድረጓን የቻይና ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
 
ኤምባሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ፥ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያ ያደረገዉ አስቸኳይ የሰብዓዊ ርዳታ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ወገኖች እየተከፋፈለ መሆኑን አስታውቋል፡፡
 
በሰሜን ኢትዮጵያ በርካታ ተፈናቃዮች መኖራቸውን የገለፀው ኤምባሲው፥ ዜጎች ለከፋ ችግር እንዳይጋለጡ የቻይና መንግስት 2ሺህ 160 ቶን አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍ ሁለቱ ሀገራት ያላቸዉን ጥልቅ ወዳጅነት የሚያመለክት መሆኑን ኤምባሲው በጋዜጣዊ መግለጫው ጠቁሟል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.