Fana: At a Speed of Life!

ተቋማቱ “ኑ የፈረሰውን የትውልድ ማፍሪያ ተቋም መልሰን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ የገቢ ማሰባሰቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የገቢ ማሰባሰቢያ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ናቸው ስምምነቱን የተፈራረሙት፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው ሙሉ በሙሉ የወደሙትን 1 ሺህ 90 ትምህርት ቤቶች ፣ 3 ዩኒቨርስቲዎች እና 3 ኮሌጆችን መልሶ ለመገንባት የሚውል መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ አካለት ኢትዮ ቴሌኮም ያዘጋጃቸውን የክፍያ አይነቶች የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይፋ አድርገዋል።

የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ማንኛውንም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የባንክ ሒሳብ ቁጥር 1000448700945፣ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አቅም የፈቀደውን የብር መጠን ጽፎ ወደ 9222 በመላክ፣ በቴሌብር ድጋፍ ለማድረግ የቴሌብር ቁጥር 9222ን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

በተጨማሪም በቴሌብር ዓለም አቀፍ ሀዋላ ከውጭ ሀገራት ድጋፍ ለማድረግ 0993161616 በመጠቀም እንዲሁም የተለያዩ የትምህርት ግብዓቶችን 4 ኪሎ በሚገኘው የትምህርት ሚኒስቴር ዋናው መ/ ቤት በመምጣት ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻል የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በማህሌት ተክለብርሃን

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.