Fana: At a Speed of Life!

የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የመንግሥት ተቋማት የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት የመንግሥት ተቋማት ቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያካሄደው ውይይት፥ የመንግሥት ተቋማት ዕቅድ ጥራት ያለው፣ ውጤታማ እና የጋራ እንዲሆን ያለመ ነው፡፡

ይህ ዕቅድ በፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የ100 ቀናት የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መታረም ያለባቸው ጉዳዮች እንዲለዩ እንዲሁም እንዲጨመር አጽንዖት የሰጡባቸውን ጉዳዮች ለማካተት የታቀደ መሆኑ ተነግሯል።

በመድረኩ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር የክትትልና ግምገማ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ፥ የዕቅድ አፈፃፀሙ የተሳካ እንዲሆን ለማድረግ እንደዚህ አይነት ውይይት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል። የልማት ዕቅዱ የአፈፃፀም ስርዓቱን በተሻለ ለመምራት የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።

በውይይቱ ከ22ቱም የፌዴራል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ሌሎች ባለሞያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.