Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪዎቹን ትህነግ እና ሸኔን በጋራ ለመዋጋት እንደሚሠሩ የክልሎቹ ርዕሳነ መሥተዳድሮች አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በወቅታዊ የፀጥታ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ገለጹ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሠ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ÷ የፀጥታ ጉዳይ የሚፈታውና የኢትዮጵያ አንድነት የሚረጋገጠው በጋራ ሥንሠራ በመሆኑ ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር ጋር በጸጥታና በልማት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመሥራት መስማማታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ዶክተር ይልቃል ከፋለ ÷ አሸባሪዎቹ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመከፋፈል እየሠሩ በመሆኑ ከህዝቡ ጋር በጋራ ቆመን ፅንፈኝነትን መዋጋት ይገባናል ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ÷ የአማራና የኦሮሚያ ክልል ሕዝቦች ትልቁ ፈተና ለሆነው ፅንፈኝነት እምቢ እንዲሉና ኢትዮጵያን እንዲያስከብሩ አሳስበዋል፡፡
አሸባሪዎቹን በጋራ ለመዋጋት እንደሚሠሩም ያስታወቁት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ÷ ከአሁን በፊት በነበሩ ጉድለቶች እና ጥንካሬዎች ላይ መምከራቸውንም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን አንድነት በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም እንዲሁም በአጎራባች አካባቢዎች በልማት እና በፀጥታ ጉዳይ ላይ በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውንም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
የክልሎቹ ርዕሳነ-መስተዳድሮች ፀረ ሕዝብ የሆኑ ጠላቶችን በመደምሰስ ዜጎችን ለማቋቋም በትብብር ለመስራት ግንኙነታቸውን አድሰዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.