Fana: At a Speed of Life!

አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ36 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዥ ፈጸመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የ36 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዥ ፈጸመ።
አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለህዳሴው ግድብ ኘሮጀክት ግንባታ በየዓመቱ ቦንድ በመግዛት ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ምስክር ነጋሽ ተናግረዋል፡፡
የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር ዛሬ የፈጸመው የ36 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዥ የሉዓላዊነት መገለጫ አንዱ ለሆነው ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የጽናት አርማችን የተሳሳተ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን የሻረ የኢትዮጵያውያን የትብብርና አንድነት ማሳያ ግድብ ነው ያሉት ሃላፊው፥ ግድቡ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ትብብር የሚገነባ ግድብ ነው ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን 3 ነጥብ 21 ቢሊየን በላይ ብር በቦንድ ግዢና በተወሰነ በስጦታ መሰብሰቡንም ተገልጿል፡፡
በዘንድሮ በጀት ዓመት 7 ወራት ውስጥ 104 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
የታላቁ ህዳሴ ኘሮጀክትን ለፍጻሜ ለማብቃት መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረባቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.