Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ነገ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማ ነገ እንደሚጀመር የበጎ ሰው ሽልማት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ፡፡
ድርጅቱ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ፥ ባለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያ በጎ የዋሉና ያሰቡ ኢትዮጵያውያን በሀገር አቀፍ ደረጃ እውቅና ሲሰጥ መቆየቱ ተመላክቷል።
አርቲስት ሰርጸ ፍሬስብኃት፥ የበጎ ሰው ሽልማት የ10 አመታት ሂደት በአዎንታዊ እና በአሉታዊ የተስተዋሉ ጉዳዮችን በሚዳስስ መልኩ የሚዘክሩ ጉዳዮች እንደሚካሄዱ ተናግረዋል።
የበጎ ሰው ሽልማት የእጩዎች ጥቆማም ከነገ አርብ እስከ መጋቢት 03 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ለአንድ ወር እንደሚቆይ ኢዜአ ዘግቧል።
የእውቅና ሽልማቶቹ በ10 ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረጉ መሆኑም ተገልጿል፡፡
ይህም በመምህርነት፣ በሳይንስ፣ በኪነጥበብ፣ ፊልም ዳይሬክቲንግ፣ በበጎ አድራጎት፣ ቢዝነስና ስራ ፈጠራ፣ ቅርስ ጥበቃ እና ባህላዊ ጥናት፣ በማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት፣ መንግስታዊ ተቋማት እና ለኢትዮጵያ እድገት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ብለዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.