Fana: At a Speed of Life!

9ኛው አገር አቀፍ የኀብረት ሥራ ኢግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምራችና ሸማች ኀብረት ስራ ማህበራት መካከል ያለምንም ጣልቃ ገብነት ቀጥተኛ የግብይት ትስስር የሚፈፀምበት 9ኛው አገር አቀፍ የኀብረት ሥራ ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፈተ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ቢሮ ጏላፊ አቶ አደም ኑሩ÷ በኀብረት ሥራ ማኀበራት የሚቀርቡ የግብርና ምርቶች ከ20 እስከ 100 ፐርሰንት የዋጋ ቅናሽ ይኖራቸዋል ብለዋል።
የኀብረት ሥራ ኮሚሽነር ተወካይ አቶ ዳሬቦ ቡሴር በበኩላቸው፥ ኢግዚቢሽንና ባዛሩ የአገር ውስጥ የግብይት ድርሻን ከማሳደጉ በተጨማሪ ኅብረት ሥራ ማህበራት ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ እና እርስ በርስ እንዲደጋገፋ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።
በኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን አዘጋጅነት ከየካቲት 3 እስከ 7 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል በሚቆየው የግብይት መርሀ ግብር÷ 150 የኀብረት ሥራ ማህበራት የግብርና ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ያቀርባሉ ይላል ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.