Fana: At a Speed of Life!

መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ውድመትና ዘረፋ የደረሰበት መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ዳግም ተደራጅቶ በመጀመሪያው ዙር ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውዴ፥ ተማሪዎችን መቀበል የተጀመረው ቅደመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ቡድን ውድመትና ዘረፋ ቢደርስበትም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በተደረገው ርብርብ ዳግም የመማር ማስተማር ስራውን ለመጀመር ከትናንት ጀምሮ ተማሪዎችን እየተቀበለ መሆኑን አስታውቀዋል።

አሁን በመጀመሪያው ዙር ከ3 ሺህ የሚበልጡ የአንደኛ፣ የሶስተኛና የአራተኛ ዓመት ተማሪዎችን ለማስተናገድ መቀበል መጀመሩን የተናገሩት ዶክተር ታምሬ፥ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ደግሞ የቀሪ ተማሪዎች ቅበላ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.