Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሕብረትና የአለም ሠራተኞች ድርጅት በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ሕብረትና የአለም ሠራተኞች ድርጅት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የአለም ሠራተኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ረዳት ዋና ዳይሬክተር ሲንቲያ ሳሙኤል ኦሎንጁን በአፍሪካ ሕብረት የጤና፣ የሰብአዊ መብትና የማህበራዊ እድገት ጉዳዮች ኮሚሽነር ሚናታ ሴሱማ ሰማቴ ጋር መፈራረማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከአፍሪካ ሕብረት ጋር የረጅም ጊዜ ትስስራችንን የሚያጠናክር ስምምነት ተፈራርመናል ሲሉ የአለም ሠራተኞች ድርጅት የአፍሪካ ቀጠና ረዳት ዋና ዳይሬክተር ሲንቲያ ሳሙኤል ኦሎንጁን ተናግረዋል፡፡

ስምምነቱ በአፍሪካ አህጉር ሊተገበር የታቀደውን የ2063 አጀንዳ ለማስፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋልም ብለዋል፡፡

የተመድ የ2030 ቀጣይነት ያለው የእድገት አጀንዳን እንዲሁም ለሁሉም አፍሪካውያን ማኅበራዊ ፍትህን ማስፈን የሚለውን የ2019ኙን የአቢጃን አዋጅ ለማስፈጸም ያግዛል ሲሉም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.