Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ የግማሽ ማራቶን ውድድር በኤርትራ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምስት ሀገራት የተሳተፉበት የምስራቅ አፍሪካ የግማሽ ማራቶን የአትሌቲክስ ውድድር በኤርትራ ምጽዋ ከተማ ዛሬ ማለዳ ተካሄደ።
በዚህ የምስራቅ አፍሪካ የግማሽ ማራቶን ውድድር ከኤርትራ፣ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ታንዛኒያ የተወከሉ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

በወንዶች ውድድር ኤርትራዊው አትሌት ሳምሶን አማረ   ሲያሸንፍ፥  ኦሎምፒያኗ አትሌት ናዝሪት ወልዱ የሴቶች ውድድርን  አሸንፋለች።

የምስራቅ አፍሪካ የግማሽ ማራቶን ውድድርሩ የተካሄደው የፈንቅል ኦፕሬሽን 32ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ መሆኑን የኤርትራ መንግስት የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.