Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎችን አባላትና ሰብሳቢዎች ምርጫ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጉባኤ በዛሬ ውሎው የምክር ቤቱን ቋሚ ኮሚቴዎች አባላትን እና ሰብሳቢዎችን ምርጫ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ምርጫውን ያጸደቀው፥ በቀረቡለት የ7 ቋሚ ኮሚቴዎች አባላት እና ሰብሳቢዎች ዝርዝር ላይ ውይይት ከደረገ በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት፥ የተከበሩ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ የሰላም፣ ፍትህ እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የተከበሩ አቶ ጋትወች ወርድየው የመንግስት በጀትና ወጪ አስተዳደር ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የተከበሩ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር የማህበራዊ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው በምክር ቤቱ ተመርጠዋል፡፡
እንዲሁም የተከበሩ ወ/ሮ አቶሜ አበበ የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የተከበሩ አቶ ማሾ ኦላና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጉዳዮች ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የተከበሩ ወ/ሮ ልእልቲ ግደይ ረዳ የመሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ፤ የተከበሩ አቶ በላይ ደጀን የከተማ ልማትና፣ ኮንስትራክሽን እና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋ/ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው መመረጣቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ የቀረቡ ዕጩዎችን አጽድቋል፡፡
በዚሁ መሠረት ወ/ሮ ሂክማ ሀይረዲን የቦርድ ሠብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
እንዲሁም አቶ በቀለ ሙለታ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈፃሚ የቦርዱ አባልና ፀሀፊ ሆነው በምክር ቤቱ ሹመታቸው ፀድቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.