Fana: At a Speed of Life!

መቀመጫቸውን አዲስአበባ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየተሠጠ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጎረቤት ሀገራት እና የኢጋድ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻውል፥ በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን በርካታ እርምጃ መውሰዱን ገልፀዋል።

ሆኖም አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት አሁንም ለአሸባሪው ህወሓት በመወገን የኢትዮጵያን ስም እያጠፉ ነው ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ከዚህ ቀደም በአማራና አፋር ክልሎች ካደረሰው ውድመት ባሻገር አሁንም በአብአላ በኩል በከፈተው ወረራ በርካቶችን ለሞትና መፈናቀል መዳረጉን አስረድተዋል።

ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብዓዊ እርዳታዎችም እንዳይደርሱ እንቅፋት መፍጠሩን ያነሱ ሲሆን፥ መንግሥት ለሰላም ካለው ፅኑ አቋም የተነሳ ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር ሀገራዊ ምክክር ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ የሚካሄድ ቢሆንም የአሸባሪው ህወሓት ኃይሎች ላጠፉት ጥፋት ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል።

ኢትዮጵያ በውስጧ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እንዲፀና ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን መልካም ወዳጅነት በማጠናከር ሚናዋን ትወጣለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጀኔራል ቡልቲ ታደሰ አሸባሪው ህወሓት የተሳሳተ መንገድ በመከተል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢሞክርም በጀግኖች የኢትዮጵያ ኃይሎች መክሸፉን አንስተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.