Fana: At a Speed of Life!

የአርሲ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 18 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርሲ ዞን በምሥራቅ ባሌ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 18 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ።

በአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሳ ፉሮ የተመራ ቡድን ድጋፉን በጊኒር ከተማ በመገኘት አስረክቧል፡፡

የባሌ ህዝብ በፀረ ጭቆና ትግል ውስጥ በሀገሪቱ እኩልነትና አንድነት እንዲረጋገጥ ፈር ቀዳጅ በመሆን የታገለ መሆኑን አቶ ሙሳ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅቱ አስታውሰው፥ ሲቸገር ከጎኑ መሆን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በችግር ወቅት ያላቸውን የመረዳዳት የቆየ ባህል አሁንም እንዳለ በተግባር ለማረጋገጥ ሌላው የድጋፉ ዓላማ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ዞኑ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ያደረገው ድጋፍ 18 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ግምት ያለው 6 ሺህ ኩንታል ምግብን ያካተተ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ችግሩ እልባት እስኪያገኝ ድረስ የጀመሩትን ሰብዓዊ ድጋፍ በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አደረጃጀቶችና ነዋሪውን ህዝብ በማስተባበር ቀጣይነት እንደሚኖረውም አረጋግጠዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የምስራቅ ባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እሸቱ በቀለ በበኩላቸው፥ በችግር ጊዜ ከጎናችን ለቆመው የአርሲ ዞን አስተዳርር በተጎጂዎች ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዞኑ አምስት ቆላማ ወረዳዎች ውስጥ 370 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የክልሉ መንግሥት የአስቸኳይ የምግብ እህል እርዳታ እያደረገ መሆኑን የዞኑ አደጋ መከላከልና የልማት ተነሺዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሀረግነሽ አለሜ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.