Fana: At a Speed of Life!

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን 478 ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 478 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንዲሁም በተለያዩ የትምህርት መስኮች በቅድመ እና ድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎችን ነው ያሰመረቀው፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራ በተጨማሪ የአካባቢውን አርብቶ አደርና ከፊል አርሶ አደር ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር በሽር አብዱላሂ ÷ዩኒቨርሲቲው በድህረ ምረቃው ዘርፍ የተለያዩ የማስፋፋት ስራዎች እየተሰራ እንደሆነ የገለፁ ሲሆን÷ የዶክትሬት መርሀግብር ለመጀመርም የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች በማከናወን ላይ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑ ገልፀው በቀጣይ ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.