Fana: At a Speed of Life!

ወደ መሀል ሀገር ሊገቡ የነበሩና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሃኒቶች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማረጋገጫ ፈቃድ የሌላቸውና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መድሀኒቶች በሲሚንቶ ጭነት ስር ደብቆ ወደ መሀል ሀገር ለማስገባት የሞከረ አሽከርካሪ ትናንት ምሽት በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

ሽከርካሪው በኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ መድሀኒቱን በመደበቅ ከሀረር ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እንዳለ በጭሮ ኬላ በተካሄደ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የጭሮ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ካሳሁን ባይሳ ተናግረዋል፡፡

ለራስ ምታትና ጀርባ ህመም እንዲወሰዱ የተዘጋጁ፣ የማረጋገጫ ፈቃድ የሌላቸውና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሀኒቶች በፍተሻው መያዛቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የተያዙት አምስት ቦንዳ መድሀኒቶች ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው መሆኑም ተገልጿል።

አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑን ዋና ሳጅን ካሳሁን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.