Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዶች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ከ29 ቢሊየን ዶላር በላይ እንደሚያጡ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማህበር አየር መንገዶች በፈረንጆቹ 2020 በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ 29 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር እንደሚያጡ አስጠነቀቀ።

ማህበሩ ከአስር ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የአየር ትራንስፖርት ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል ሲል ትንበያ አስቀምጧል።

በዚህም በዋናነት በእስያ ፓሲፊክ የሚገኙ አየር መንገዶች ተጎጅ ይሆናሉም ነው ያለው።

ይህም የኮሮና ቫይረስ የፈጠረውን ስጋት ተከትሎ ሃገራት የሚያደርጉትን በረራ በመቀነሳቸው የሚፈጠር መሆኑንም አስረድቷል።

ይህን ተከትሎም በእስያ ፓሲፊክ የሚገኙ ሃገራት አየር መንገዶች 27 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ሊያጡ እንደሚችሉም አስታውቋል።

ከእስያ ውጭ ያሉ ሃገራት አየር መንገዶች ደግሞ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ እንደሚገጥማቸውም ነው የገለፀው።

ከዚህ ባለፈ ግን ቻይና ከዘርፉ 12 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር ታጣለችም ነው ያለው ማህበሩ ባወጣው መግለጫ።

ማህበሩ ትንበያውን በፈረንጆቹ 2003 ተከስቶ የነበረው የሳርስ ቫይረስ ያስከተለውን ጉዳት መሰረት አድርጎ ማውጣቱንም አስረድቷል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.