Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት የጥገና ሂደትን ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ 144 ዓመት እድሜ ያለውንን የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት የጥገና ሂደትን ተመለከቱ።
ከ2012 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ጥንታዊ ቤተ መንግስቱ እድሳት እየተደረገለት ይገኛል።
የጅማ የአባ ጅፋር ቤተመንግሥት በውስጡ አራት ህንፃዎች ያሉት ሲሆን፥ ዋና ቤተመንግስት፣ የቤተሰብ መኖሪያ፣ የማህበረሰብ መስጂድ እና የቤተሰብ መስጂድ የሚባሉት ናቸው አራቱ ህንፃዎች።
እድሳቱ የተጀመረው ከቤተሰብ መኖሪያ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት የ14ቱም ልጆቻቸው መኝታ ክፍሎች ተጠግነው ተጠናቀዋል።
ዋና ቤተመንግሥት አንደኛ ወለል የበረንዳ ወለል በስተምስራቅ ሰሜን እና ደቡቡ የተጠናቀቁ ሲሆን፥ ሌሎቹ የቤተመንግስቱ አካላት ጥገናቸው አልተጀመረም።
ጥገናው የተጀመረው በእድሜ ብዛት እጅግ ከተጎዱ የቤተመንግሥቱ ክፍሎች እንደሆነም በጉብኝቱ ላይ ተገልጿል።
የጅማ አባጅፋር ቤተመንግሥት በ1870 ዓመተ ምህረት ነው ግንባታው የተጠናቀቀው።
በአልአዛር ታደለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.