Fana: At a Speed of Life!

ዓለም አቀፉ የሬዲዮ ቀን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሬድዮ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉ የሬዲዮ ቀንን አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሬድዮ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉ የሬዲዮ ቀንን እያከበሩ ይገኛሉ፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ በዚህ ፥ ወቅት ሬድዮ ህብረተሰቡን በማንቃትና መረጃን ተደራሽ በማድረግ በኩል ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

በተለይ በኢትዮጵያ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ለመረጃ ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወቱንም አንስተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት በአገር ብሎም በህዝብ ሰላምና መረጋጋት ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑን አቶ መሐመድ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ይህንን ድርጊት በህግ አግባብ ለማስተካከል ከሚደረገው ጥረት ባሻገር መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን መከላከል እንደሚጠበቅባቸው ነውበ የተናገሩት፡፡

ዓለም አቀፍ የሬዲዮ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ11ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ3ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.