Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ዝግጅት ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
 
በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋና አቻው ጋር ለሚጫወተው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ነው አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ለ27 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉት።
 
ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ያደረጋቸውን አራት የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታዎች በድምር ውጤት አሸናፊነት በመወጣት በቀጣይ ከጋና አቻው ጋር ለሚያደርገው የ5ኛው እና የመጨረሻው የማጣርያ ዙር ጨዋታ ያደርጋል፡፡
ለጨዋታዉ ዝግጅት የተጠሩ ተጫዋቾች ሰኞ የካቲት 7/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የብሔራዊ ቡድን የስፖርት ትጥቃቸውን በመያዝ በኢትዮጵያ እግር ኳሰ ፌዴሬሽን ፅሕፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.