Fana: At a Speed of Life!

ንግድ ባንክ ያስገነባው አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባውን አዲስ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ዛሬ እመርቋል፡፡
 
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ ደንበኞች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተኝተዋል።
 
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በምረቃ መርሃ ግሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷የባንኩን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ምረቃ እና የባናኩን 80ኛ ዓመት በዓል ለማክበር ለተገኙ እንግዶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ንግድ ባንኩ በ80 ዓመት ጉዞው የቁጠባ ባህል እና ግንዛቤን በማሳደግ ለደንበኞቹ አስፈላጊውን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አውስተዋል፡፡
 
ባንኩ ከጊዜው ጋር የሚዘምኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለደንበኞቹ ቀልጣፋ እና አስተማማኝ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፡፡
 
በማህበራዊ አገልግሎትም ባንኩ እና ሰራተኞቹ ለህልውና ዘመቻው እንዲሁም ለሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች በርካታ ድጋፎች ማድረጉን ነው የገለጹት።
 
ባንኩ በጥሩ የፋይናንስ መሰረት ላይ የተገነባ በመሆኑ ዘላቂነቱን ለማስጠበቅ ደንበኞች አጋርነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳሰበዋል፡፡
 
አዲሱ ህንጻ 209 ነጥብ 15 ሜትር ከፍታ ያለው መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ ÷ ለግንባታውም 303 ሚሊየን 500 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወጪ መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
 
በውስጡም የቢሮ አገልግሎት ከሚሰጡ ክፍሎች በተጨማሪ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ሙዚየም እና ሲኒማ ቤትን ያካተተ ሲሆን፥ እስከ 1 ሺህ 500 መኪናዎችን መያዝ የሚችል ማቆሚያም ያለው መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
የህንጻ ፕሮጀክቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ ጉልህ ሚና ለተጫወቱ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የህንጻውን ውስጣዊ እና ውጫዊ ገጽታ ለመመልከት ሊንኩን ይጫኑ፡-
 
https://www.youtube.com/watch?v=aK_EBu7K5Wg
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.