Fana: At a Speed of Life!

ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣ የአይነት ድጋፍ ለቆቦ ከተማ ተጎጂዎች ተከፋፈለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአይዞን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ከዳያስፖራው በተሰባሰበው ገንዘብ የተገዛ የመጀመሪያው ዙር ድጋፍ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ ለሚገኙ ተጎጂዎች ተከፋፍሏል::
 
ድጋፉ የአማራ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ እታገኘሁ አደመ፣ የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳዳሪ ዲያቆን ተስፋሁን ባታቢል እንዲሁም የኢትዮጵያ ዳያስፕራ ኤጀንሲና የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ሰራተኞች በተገኙበት ነው የተከፋፈለው፡፡
 
የተደረገው ድጋፍ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ ያካተተ ሲሆን÷ ይህም ከ40ሺ በላይ ለሚሆኑ ተጎጂዎችን መከፋፈሉን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በድጋፉ ከ18 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ 4ሺ 590 ኩንታል ሩዝና ዱቄት እንዲሁም ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁስ መካተታቸው ተገልጿል፡፡
በቀጣይም በሁለቱ ክልሎች ለሚገኙ ሌሎች አካባቢዎች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ኤጀንሲው ጠቁሟል፡፡
 
በአይዞን ኢትዮጵያ እስከአሁን ከ7 ሚሊየን ዶላር በላይ የተሰበሰበ ሲሆን÷ ድጋፉም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥረታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.