Fana: At a Speed of Life!

ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገት የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉ 5 የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ተሸለሙ

አዲስ አበባ፣የካቲት 6፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ዕድገት የላቀ አስተዋፅኦ ያደረጉ አምስት ግለሰቦች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የላቀ አገልግሎት ሽልማት ተሰጣቸው።
 
የተሸለሙት 5 የኢኮኖሚ ባለሙያዎች አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፣ ዶክተር ተፈራ ደግፌ፣ አቶ አለሙ አበራ እና አቶ ጥላሁን አባይ ናቸው።
 
ባለሙያዎቹ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን በመቅረፅ እና በማሰፈፀም፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእድገት ጉዞ ላይ የሪፎርም ስራዎች ላይ በመሳተፍ የላቀ አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
 
በተጨማሪም ባለፉት ጊዜያት የተዛባዉን የሀገሪቱ ማክሮ አኮኖሚን ከለውጡ መንግስት ጋር በመሆን ኢኮኖሚው እንዲረጋጋ እገዛ ስለማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
 
በተለይ በፋይናንሱ ዘርፍ የመንግስት የልማት ድርጅቶች እዳቸዉን በጊዜ ባለመክፈላቸዉ የንግድ ባንከ የፋይናንስ አቅም በተጎዳበት ወቅት ባንክን ብድር በማስመለስ መልሶ የፋይናንስ አቅሙ እንዲጎለበት እነዚህ ባለሙያዎች ሙያዊ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
 
የንግድ ባንክ የቦርድ አመራር እንዲሸለሙ ያቀረባቸ እነዚህ የኢኮኖሚ ባለሙዎች ተዘጋጀላቸውን የእውቅና ሽልማት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተቀብለዋል።
 
በሚኪያስ አየለ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.