Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል መደበኛ የልማት ሥራ ሊያሠራ የሚያስችል የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አለ- የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ሁኔታ በአንጻራዊነት የተረጋጋና ሰላም የሆነበት መደበኛ ሥራዎችን መሥራት የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩን የክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተናገሩ።
በክልሉ የሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኽምራ፣ ሰሜን ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎች በህወሓት የሽብር ቡድን ተወረው በነበረበት ወቅት የሕዝቡ መሰረታዊ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ችግር ውስጥ ገብቶ እንደነበር ገልጸው፥ በአሁኑ ወቅት ከውስን አካባቢዎች በስተቀር ነጻ ሆነው መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡
ከወረራ ነጻ በሆኑ አካባቢዎች የልማትና መልሶ የማቋቋም ሥራ መሥራት የሚያስችል ሰላም መፈጠሩን የገለጹት አቶ ግዛቸው፥ የተፈጠረውን አንጻራዊ የሰላም ሁኔታ የበለጠ በማረጋገጥ የልማት ስራዎች የሚሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም የአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኃይል በነበረባቸው አካባቢዎች ሰላም እንዲሰፍን ክልሉ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው÷ የአማራ ክልል በሚዋሰንባቸው አካባቢዎች ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በመገምገም አስተማማኝ ሰላም በክልሉ ለማስፈን እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሕግና ስርዓት እንዲሰፍን ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት ናቸው ያሉ ሲሆን፥ የክልሉ አዋሳኝ በሆኑ አካባቢዎች ለሚፈጠሩ ችግሮች እልባት ለመስጠትም ከሰሞኑ ከክልል ዕርሳነ መስተዳድሮች ጋር ውይይት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.