Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች 20 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል 20 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የደብቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ለኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡
 
ድጋፉ በክልሉ ቦረና እና ጉጂ ዞኖችበተከሰተው ድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚውሉ የተለያዩ ምግብ ነክ ቁሳቁስን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
በተጨማሪም ድጋፉ በአካባቢዎቹ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው እንስሳት የሚውል መኖ ያካተተ መሆኑን ከኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.