Fana: At a Speed of Life!

የመንገዶች ባለስልጣን ያስገነባውን ቋሚ የማሳያ ማዕከል አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያስገነባውን ቋሚ የማሳያ ማዕከል አስመረቀ።

ማዕከሉ የተቋሙን የታሪክ ሂደት፣ ለሀገር ያበረከተውን አስተዋጽኦ እና በየዘመኑ የነበሩ ሂደቶችን በሰነድ እና በቁስ አካላት አካቶ የያዘ ነው።

በተጨማሪም የተቋሙን ሙሉ ታሪክ በፎቶ በማደራጀት እንዲሁም ተቋሙ እስካሁን በመንገድ ግንባታ ሂደት ያለፈባቸውን መንገዶች የሚያሳዩ ታሪካዊ ዘጋቢ ፊልሞችንም ያካተተ ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በቀጣይ ኢትዮጵያ በመንገድ ልማት ዘርፍ ልትደርስበት የሚገባትን ዕራይ የሚያመላክቱ ግብአቶች በማዕከሉ ተካተዋል ነው የተባለው።

ቋሚ ማዕከሉ የአውራ ጎዳና ከምስረታ ጀምሮ በየጊዜው የነበረውን አበርክቶዎች ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ የጎላ ሚና እንደሚያበረክት የተቋሙ ዋና ዳሬክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ ገልጸዋል።

ማዕከሉ ለውጭም ሆነ ለሃገር ውስጥ ጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚያገለግልም ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.