Fana: At a Speed of Life!

በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ሩሲያ ለተጨማሪ ውይይት ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ያለውን ውጥረት ለማርገብ ከምዕራባውያን ጋር ተጨማሪ ውይይት ለማድረግ በሯን ክፍት ማድረጓን አስታወቀች፡፡
ሞስኮ ስታደርጋቸው የነበሩ ወታደራዊ ልምምዶች መጠናቀቃቸውን የቀሩትም በቀጣይ እንደሚያበቁ ነው የገለጸችው፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደገለጹት፥ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለአሜሪካ እና ለኔቶ ደኅንነት የሰጠችው የዋስትና ማረጋገጫ ሀሳብ በምዕራባውያን ተቀባይነት እያገኘ ነው፡፡
ቭላድሚር ፑቲን ለድርድር እና ለውይይት ዝግጁ መሆናቸውን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ÷ የዩክሬን ጉዳይ የሩሲያን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ሞስኮ ደኅንነቷን የምታረጋግጥባቸው ሀሳቦች ላይ ፑቲን ለመስማማት ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ከአሜሪካ እና ከኔቶ በተሰጡ ምላሾች ላይ ባደረጉት ውይይት፥ በዩክሬን ጉዳይ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለመስማማት ሁልጊዜ እድል አለ ማለታቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧ፡፡
በውይይታቸውም÷ ዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ስጋቶችን በመቀነስ ረገድ የተሻሻሉ ሀሳቦችን ማቅረቧን እና የአውሮፓ ሕብረት እና የኔቶ ወታደራዊ ጥምረት ምላሾች ግን አጥጋቢ እንዳልሆኑ ላቭሮቭ ለፑቲን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.