Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ጋር ውይይት አደረገ፡፡

በዚህም ወቅት በመስቀል አደባባይና በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት ቦታዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ የጋራ ውይይት መደረጉ ነው የተመለከተው።

ውይይቱ በፍጹም ቅን ልቡና፣ መደማመጥና መግባባት በተሞላበት ስሜት መካሄዱን አስተዳደሩ አስታውቋል።

በውይይቱም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመስቀል አደባባይና የጃንሜዳ ባሕረ ጥምቀትን በተመለከተ የተነሱትን ጥያቄዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የጋራ ኮሚቴ በማቋቋም ቀጣይ ውይይቶችን መሠረት በማድረግ የማያዳግም ምላሽ ለመስጠት የጋራ ስምምነት ላይ ተደርሷል ተብሏል፡፡

ወደፊትም ቤተ ክርስቲያንና የከተማ አስተዳደሩ በልማት፣ በሰላምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.