Fana: At a Speed of Life!

በዞኑ አሸባሪው ህወሓት ባደረሰው ጉዳት የውሃ ሽፋኑ ከነበረው ሽፋን 10 በመቶ ዝቅ ብሏል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን አሸባሪው ህወሓት በውሃ ተቋማት ላይ ባደረሰው ጉዳት የውሃ ሽፋኑ ከነበረው 64 በመቶ ወደ 54 በመቶ ዝቅ ማለቱን የዞኑ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት መምሪያ ገለፀ።
በዞኑ አጠቃላይ 14 ሺህ 372 የውሃ ተቋማት እንደነበሩ የገለፁት የመምሪያው ተወካይ ሀላፊ አቶ ንጉስ ተፈራ፥ በወረራው ምክንያት 672 በገጠር እና 56 በከተማ የሚገኙ የውሀ ተቋማት በከፊል እና ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ብለዋል።
የውሃ ተቋማቱ የጉዳት መጠንም ከ30 እስከ 70 በመቶ መሆኑን ጠቁመው፥ ውድመቱ በንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚዎች ላይ ችግር የፈጠረ ሲሆን ተቋማቱን ለመጠገን ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ባቀረባቸው ሶስት ጀኔሬተሮች የውሃ ጉድጎዶችን መጠቀም ቢጀመርም በቂ ባለመሆኑ መንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ድጋፍ እንዲያድርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአንድነት ናሁሰናይ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.