Fana: At a Speed of Life!

222 ሺህ 740 ሄክታር መሬት በቅመማ ቅመም ዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢትዮጵያ 222 ሺህ 740 ሄክታር መሬት በቅመማ ቅመም ዘር መሸፈኑ ተገለፀ፡፡
በዓለማችን የቅመማ ቅመም አምራች ከሆኑ አገራት ኢትዮጵያ በቀዳሚነት የምትገኝ ሲሆን ፥ በርካታ የቅመማ ቅመም ዝርያዎችንም ታበቅላለች፡፡
ከዚህም ውስጥም አብዛኛውን ወደ ውጭ ትልካለች ነው የተባለው፡፡
በዓመት 244 ሺህ ቶን ቅመማ ቅመም እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ምርት ገበያው የኢትዮጵያን የግብርና ምርቶች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ ግብይት እንዲካሄድባቸው በማስቻል በምርት ጥራትና እመርታ ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጿል፡፡
ይህንንም ለማጎልበት በ2014 ዓም አራት አይነት የቅመማ ቅመም ምርቶችን ወደ ዘመናዊ ግብይት ስርዓቱ ማስገባቱን ጠቁሞ ፥ እነሱም አብሽ፣ ቁንዶ በርበሬ፣ ድንብላልና ጥቁር አዝሙድ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.