Fana: At a Speed of Life!

የብልፅግና አመራሮች የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ ናቸው – ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልፅግና አመራሮች የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ተናገሩ።
ዶክተር ቢቂላ ይህንን ያሉት ከፋና ዜና መጽሄት ጋር የስልክ ቆይታ ባደረጉበት ወቅት ነው።
ከሰሞኑ የከፍተኛ አመራሮችን አቅም የሚገነባ ስልጠናዊ ግምገማ አመራሩ በእውቀት፣ ክህሎት፣ ስነምግባር እና አስተሳሰብ ህዝቡ በሚፈልገው ደረጃ ብቁ ይሆን ዘንድ ታስቦ የተካሄደ መሆኑን አንስተዋል።
አመራር ስራውን በውጤት ብቻ እንዲመዝን፣ ወጪ ቆጣቢ አሰራርን እንዲከተል፣ በእቅድ እንዲመራ እና ለህዝቡ ቅርብ እንዲሆን በመድረኩ ከስምምነት የተደረሰባቸው ጉዳዮች ናቸው ነው ያሉት።
ብልፅግና በቀጣይነት ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ህዝቡ ችግሮችን ከመለየት እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ከመጠቆም አንጻርም እንደተለመደው እገዛውን እንዲቀጥል ዶክተር ቢቂላ አሳስበዋል።
አመራሩ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን የሚያጸና፣ ኢትዮጵያዊያንን የሚያሰባስብ፣ የትብብር እና የወዳጅነት ስሜት እንዲያብብ ጠንክሮ የሚሰራ እንዲሁም ከጽንፈኝነት እና ራስ ወዳድነት የራቀ ሊሆን እንደሚገባም ነው ያስታወቁት።
በአፈወርቅ አለሙ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.