Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ለዞንና ከተማ አስተዳደሮች 17 ተሽከርካሪዎችን ለገሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ጨምሮ ለሁሉም ዞኖች እና ለአዲስ ከተሞች ፅህፈት ቤቶች የ17 ተሽከርካሪዎች ድጋፍ አደረገ።
የጽህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ግርማ የሽጥላ በርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ፥ ፓርቲው የለገሳቸው ተሽከርካሪዎች “ሀርድ ቶፕ ዳብል ጋቢና”ሲሆኑ፥ ድጋፉም በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለማደራጀት እና ለማቋቋም በማሰብ ታስቦ የተደረገ ነው ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን ዞን ጨምሮ ሁሉም ዞኖች እና አዲስ ወደ ጂኦ ፖሊታንት ላደጉ ከተሞች የተሽከርካሪ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
አያይዘውም ለኮምቦልቻ፣ ደብረ ብርሃንና ደብረ ማርቆስ ከተሞች ድጋፍ መደረጉን አብራርተዋል፡፡
በተመሳሳይ ለሁሉም ዞኖች የፓርቲ ጽ/ቤቶች አንድ አንድ ተሽከርካሪዎች እና ለደቡብ ወሎ ዞን በልዩነት ሁለት ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ መደረጉንም ነው የተናገሩት፡፡
ተሽከርካሪዎቹ በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎችን መልሶ ለማደራጀት እና ለማቋቋም ለሚደረገው ርብርብ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ጠቁመው÷ በተጨማሪም ዞኖች የነበረባቸውን የተሽከርካሪ ችግር በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላሉ ማለታቸውን ከፓርቲው ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደር ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ከአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበር እና ከአማራ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሽጥላ እጅ ቁልፍ ተረክበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.