Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ለድርቅ ተጎጂዎች የሚሆን ተጨማሪ 2 ቢለዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ድጋፍ የሚዉል ተጨማሪ 2 ቢሊየን ብር (39 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር) ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ድጋፉ ድርቅ በተከሰተባቸዉ የአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሶማሌ ክልሎች ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች እርዳታ የሚውል ነዉም ተብሏል፡፡

በሶማሌ፣ ኦሮሚያና ደቡብ ክልሎች ሙሉ በሙሉና በከፊል በተደጋጋሚ ዝናብ ወቅቱን ጠብቆ ባለመዝነቡ እንደዚሁም በአማራ ክልል በነበረው ግጭት ምክንያት በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ለምግብ እህል እርዳታ መዳረጋቸው ይታወቃል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.