Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ወረራ እንዲሁም ከኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ጨምሮ 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች የዕለት ደራሽ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አስታወቀ።
ለእነዚሁ ድጋፍ የሚሹ ዜጎች የክልሉ መንግሥት፣ የፌደራል መንግሥት፣ ዳያስፖራው፣ የሃይማኖት ተቋማት እና ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ያልተቋረጠ ድጋፍ እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
በክልሉ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው ከነበሩት ወገኖች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸውን የኮሚሽኑ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ እታገኘሁ አደመ ተናግረዋል።
በዚህም በአማራ ክልል ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሞ ብሔረሰብ እና ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን በአጠቃላይ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው መቆየታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በህወሓት ወረራ ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ከነበሩት ዜጎች መካከል አብዛኛዎቹ ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸው ተመላክቷል፡፡
ከኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ቀደም ሲል ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል የገቡ 900 ሺህ ወገኖች እስካሁን ወደ ቀደመ መኖሪያቸው ያልተመለሱ ሲሆን÷ የክልሉ መንግሥትም እስካሁን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ወይዘሮ እታገኘሁ ገልጸዋል፡፡
ለእነዚህ ዜጎች የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው ጥሪ ያቀረቡት።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.