Fana: At a Speed of Life!

ግጭቶችን በውይይት ከመፍታት አንፃር የእምነት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው – ዶ/ር ቀነዓ ያደታ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግጭቶችን በውይይት ከመፍታት አንጻር የእምነት ተቋማት ሚና ከፍኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታ ተናገሩ፡፡

በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት “የዉይይት ዕሴት ባህልን ለማዳበር የሃይማኖት ተቋማት አስተዋፅኦ” በሚል ርዕስ የሃይማኖት አባቶች ዉይይት ተካሂዷል፡፡

በዉይይት መድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና የሚመለከታቸው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ቀነዓ ፥ የእምነት ተቋማት ዜጎች መልካም ስነምግባር እንዲኖራቸው ከማድረግ አንጻር ከፍተኛ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ጠቁመው ፥ ዛሬ የተጀመረው የውይይት መድረክ ለአካታች ሀገር አቀፍ ውይይት ጥሩ ግብዓት ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው ፥ የየዕለት ማሕበራዊ ክንውን አካል በማድረግ ችግሮችን በየደረጃው የሚፈቱበት ባሕልን የሚያዳብር እንደሆነ ጠቅሰው ፥ የሃይማኖት ተቋማት አስተዋጽኦም ወሳኝ እንደሆነ አንስተዋል።

በውይይት መድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰፋ ያለ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በዛሬው እለት የተጀመረው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ለተወጣጡ የሃይማኖት አባቶች በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የሚያደርገው የውይይትና የምክክር መረሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት ወር ማብቂያ ድረስ የሚቀጥል መሆኑም ከከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.