Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ድሎ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ከ29 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቦረና ዞን ድሎ ወረዳ በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ከ29ሺህ 400 በላይ ሰዎች እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ረሺድ ኢብሬን ተናገሩ፡፡

ለተጎጂዎች በአሁኑ ሰዓት እየተከፋፈለ ያለው የስንዴ፣ የፋፋ እና የሩዝ አቅርቦት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በወረዳው ካሉ 69 ሺህ 720 ሰዎች እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ63 ሺህ 900 በላይ ናቸው ያሉት አስተዳዳሪው ፥ ከዚህ ውስጥ ከ20 ሺህ በላዩ እርዳታ ያልደረሳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከነዚህ ውስጥ ወደ 15ሺህ 500 የሚሆኑትን በመለየት እርዳታ ለማድረስ መንግስት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡

ድሎ በዞኑ ከሚገኙ 13 ወረዳዎች አንዱ ሲሆን፥ ድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት በማድረሱ አብዛኛው ህዝብ ድጋፍ ፈላጊ ሆኗል፡፡

ድርቁ ህፃናትን ጨምሮ፣ እናቶች እና አዛውንቶች ለምግብ እጥረት እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል፡፡

አብዛኞቹም ድርቁ የከፋ ጉዳት አድርሶባቸው በህክምና እንዲያገግሙ እየተደረገ መሆኑንም ነው አሰተዳዳሪው የጠቀሱት፡፡

የድሎ መጋላ ጤና ጣብያ ዳይሬክተር አብርሃም አበበ በበኩላቸው፥ ለህፃናቱ የሚደረጉ የኤፍ-100 እና የኤፍ -75 አልሚ ምግቦች አቅርቦት በቂ ባለመሆኑ በህፃናቱ ላይ ጉዳቱ እየከፋ እንዳይመጣ ስጋት አለን ብለዋል፡፡

ለዚህም መንግስት ከሚያደርገው እርዳታ በተጨማሪ ሌሎች አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል፡፡

በታሪኩ ለገሰና አፈወርቅ እያዩ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.